DC DMV Practice Knowledge Test (Amharic - አማርኛ)

67 Questions | Attempts: 190769

SettingsSettingsSettings
DC DMV Practice Knowledge Test (Amharic - አማርኛ) - Quiz

ይህ የመለማመጃ የእውቀት ፈተና ለዲሲ ዲኤምቪ የእውቀት ፈተና ለመዘጋጀት ይረዳዎታል። የዲሲ የነጂዎቸን የእውቀት ፈተናን በስኬታማ ሁኔታ ለማለፍ የዲሲን የመንዳት(የአሽከርካሪዎች) ማንዋል ማጥናት ግዴታ ነው። ዋናውን የነጂዎች የአውቀት ፈተና ለመውሰድ የዲሰ ዲኤምቪ የአገልግሎት ማእከል ሲመጡ፣ ለእያንዳንዱ ለተወሰደው የነጂ እውቀት ፈተና $10 ክፍያ አለው። የነጂዎች የአውቀት ፈተና የሚታይ በእጅ የሚነካ (ተች ስክሪን) ወይም በጆሮ የሚሰማ(ኦድዮ)(ሄድፎን በመጠቀም) ተች ስክሪን ያለው በኮምፕወተር ላይ የሚወሰድ ነው። በጆሮ የሚሰማውን(ኦድዮ)የሚመርጡ ከሆነ፣ ፈተናውን ከመጀመሮ በፊት የዲኤምቪ ተወካዩን ያስታውቋቸው። በዚሀ የመለማመጃ ፈተና ላይ ያሉት ጥያቄዎች በደሲ ዲኤምቪ በሚወሰደው በዋናው የነጅዎች የእውቀት ፈተና ላይ ሊኖሩ ወይም ላይኖሩ ይችላል። ፈተናውን ለመወሰድ ዲኤምቪ ከመምጣቶ በፊት የዲሲን የመንዳት(የአሽከርካሪዎች) ማንዋሉን ሙሉ በሙሉ ማጥናት እንዳለቦት ያስታውሱ። የእውቀት ፈተናውን ለማለፍ 80% ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ነጥብ ማግኘት ያስፈልጋል።  የእውቀት ፈተናውን በ12 ወራት ግዜ ውስጥ 6 ግዜ ከወደቁ፣ የመጀመሪያውን ፈተና ከወደቁበት በሃላ እስከ 12 ወራት ድረስ 7ኛውን ፈተና ለመውሰድ አይፈቀድሎትም። 


Questions and Answers
 • 1. 
  ሀይዌይ ላይ መስመሮችን (ሌንን) በመቀየር ላይ እንዳሉ:
  • A. 

   ሁልግዜ የመስመር(ሌን) መቀየርን ምልክት ማድረግ

  • B. 

   ወደሃላ ማሳያ እና የውጭ መስታዋቶች ማየት

  • C. 

   የማይታዮትን ቦታ (ብላይንድ ስፖት) ከትከሻዎ በላይ አየት በማድረግ ማረጋገጥ

  • D. 

   ሁሉም መልስ ነው

 • 2. 
  በመገናኛ መንገድ ላይ ብልጭ ድርግም የሚል ቀይ የትራፊክ መብራት ሲኖር አንድ አይነት የሚሆነው ከምን ጋር ነው፡
  • A. 

   አቁም የሚል መብራት

  • B. 

   መብራቱ ወደ አረንጓዴ ሊቀየር ነው

  • C. 

   አቁም የሚል ምልክት

 • 3. 
  መስቀለኛ መንገድ ላይ ከደረሱ እና ወደጎን እይታዎ ከተዘጋቦት፣ ማድረግ የሚገባዎት:
  • A. 

   ማቀዝቀዝ(ፍጥነት መቀነስ) እና በሁለቱም በኩል መመልከት

  • B. 

   ባሉበት ፍጥነት መቀጠል እና በሁለቱም በኩል መመልከት

  • C. 

   ማቆም፣ ከዚያ በሁለቱም በኩል በግልጽ ማየት እስኪችሉ ድረስ ቀስ እያሉ መጠጋት

 • 4. 
  ከፊቶ ለፊቶ ከሚመጣ የፊት መብራት የሚወጣ ጮራን(ነጸብራቅን) ለማስወገድ:
  • A. 

   አይኖቾትን የመንገዱ መሀከል መስመር ላይ ያተኩሩ

  • B. 

   በመንገዱ ጎኖች እና ቀጥታ ወደፊት እያቀያየሩ ይመልከቱ

  • C. 

   አይኖትን ቀጥታ ፊት ለፊት ላይ ያተኩሩ

 • 5. 
  ከጓሮ መንገድ(አሊይ) መግቢያ ወይም ከግል የመግቢያ መንገድ ምን ያህል ቀርበው ማቆም ይችላሉ?
  • A. 

   10 ጫማ

  • B. 

   20 ጫማ

  • C. 

   5 ጫማ

 • 6. 
  የሚታየው ምልክት የሚያሳየው:
  • A. 

   ከዋናው መንገድ ወጥቶ ዞሮ መሄጃ መንገድን ይፈልጉ

  • B. 

   ከፊት ለፊት የግንባታ ወይም የእደሳ ስራ ቦታ አለ

  • C. 

   በጥንቃቄ ይለፉ

 • 7. 
  የሚታየው ምልክት ትርጉሙ:
  • A. 

   የባቡር ሀዲድ እንደሚያቋርጥ

  • B. 

   እግረኛ እየተሻገረ ነው

  • C. 

   ማለፍ የማይታይበት ዞን

 • 8. 
  ይህ የእጅ ምልክት ትርጉሙ:
  • A. 

   ማቆም ወይም ማቀዝቀዝ(ፍጥንት መቀነስ)

  • B. 

   ወደ ቀኝ መታጠፍ

  • C. 

   ወደ ግራ መታጠፍ

 • 9. 
  ደርቦ ማቆም የተከለከለው ለምንድን ነው?
  • A. 

   ምክንያቱም ጠርዙ ላይ ያለው መኪና መውጣት ስለማይችል

  • B. 

   ምክንያቱም የመኪናዎችን ፍሰት(ትራፊክ) ይዘጋል እና ለአደጋዎች መንስኤ ይሆናል

  • C. 

   ጠርዝ ስለሌለ መኪናዎ ተንሸራትቶ ሊሄድ ይችል ይሆናል

 • 10. 
  ወደ ቀኝ ሲታጠፉ፣ ማድረግ ያለቦት:
  • A. 

   በመሻገሪያው ላይ ላሉት እግረኞች ቅድሚያ መስጠት

  • B. 

   እንደርሶ ወደ ቀኝ በመታጠፍ ላይ ላሉት ከፊት ላሉ ተሽከርካሪዎች ጥንቃቄ መውሰድ

  • C. 

   በእርሶ እና በመንገዱ በቀኝ በኩል መሀከል በመጓዝ ላይ ላሉ ባለብስክሌቶች ቅድሚያ ይስጡ

  • D. 

   ሁሉም መልስ ነው

 • 11. 
  የዲሲ የመንጃ ፈቃዶን በማግኘት ላይ እያሉ፣ ማድረግ የሚችሉት:
  • A. 

   ለልዩ አገልግሎት መመዝገብ

  • B. 

   የአካል(ብልት) ወይም ቲሹ ለጋሽ ለመሆን መምረጥ

  • C. 

   በምርጫ ለመምረጥ መመዝገብ

  • D. 

   ሁሉም መልስ ነው

 • 12. 
  ነጥብ የሚያሰጥ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ የሚደረግ ጥሰት ሳይኖርቦት የሚሰራ የዲሲ የመንጀ ፈቃድ ለሙሉ የካለንደር አመት ይዘው ከቆዩ፣ በመንዳት መዝገቦ ላይ ጥሩ ነጥብ (Good Point)ለማግኘት ብቁ ይሆኑ ይሆናል።
  • A. 

   እውነት

  • B. 

   ሀሰት

 • 13. 
  በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ውስጥ የሞተር ተሽከርካሪ እየነዱ እያሉ በህግ አስፈጻሚ እንዲቆሙ ቢደረጉ፣ የሚሰራ የመንጃ ፈቃድ፣ የተሽከርካሪ ምዝገባ እና የኢነሹራንስ ማስረጃ ማቅረብ ሀላፊነት ይኖሩቦታል።
  • A. 

   እውነት

  • B. 

   ሀሰት

 • 14. 
  የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ህግ ነጂው(ሹፌሩ) እና _____________ የደህንነት ቀበቶ(ሲት ቤልት) እንዲያደርጉ ያስገድዳል።
  • A. 

   ሁሉም ተሳፋሪዎች

  • B. 

   ከፊት መቀመጫ ላይ ያለ ተሳፋሪ

  • C. 

   እድሜያቸው ከ 18 አመት በታች የሆኑ ተሳፋሪዎች

 • 15. 
  የትራፊክ ምልክት መብራት አረግጓዴ ከሆነ እና የፖሊስ መኮንን(ፖሊስ) እንዲቆሙ ምልክት ካደረገሎት፣ ማድረግ ያለቦት:
  • A. 

   የትራፊክ መኮንኑን መታዘዝ

  • B. 

   የትራፊክ ምልክቱን መታዘዝ

  • C. 

   ከፊት ለፊቶ ያለው ተሽከርካሪ የሚያደርገውን ማድረግ

 • 16. 
  ሌላን ተሽከርካሪዎች ለማለፍ እንደተፈቀደሎት ከሁሉም በተሻለ መንገድ ለማወቅ ማየት ያለቦት:
  • A. 

   ብልጭ ድርግም የሚል አረንጛዴ መብራት መኖሩን

  • B. 

   ከፊት ለፊቶ ያለው መንገድ ቀጥተኛ መሆኑን

  • C. 

   ከፊት ለፊቶ ያለው ተሽከርካሪ ለማለፍ ይቻላል የሚል ምልክት ማሳየቱን

  • D. 

   የመስመሩ ቀለም የተቆራረጠ ወይም አንድ ወጥ መሆኑን

 • 17. 
  መስመሮቹን ወደ አንድ የሚቀላቅል ቦታ(ሌን) ወይም መስመር የሌለው ወደ ኢንተር-ስቴት ውስጥ የሚያስገባ አጭር መግቢያ ላይ:
  • A. 

   የመጨረሻው የቀኝ መስመር (ሌን) ላይ ይግቡና እስከ መኪኖቹ ፍሰት ድረስ ፍጥነቶን ይጨምሩ

  • B. 

   የትራፊኩ ፍጥነት ላይ ለመድረስ የዋናው መንገድ ጎን(ሾልደርን) ይጠቀሙ

  • C. 

   በትራፊኩ(በመኪኖቹ ፍሰት) ላይ ክፍተት ሲያገኙ ብቻ መግቢያው ላይ ፍጥነቶን ይጨምሩ

 • 18. 
  በመንዳት ላይ እያሉ መዘናጋት ሊፈጠር የሚችልበት ምክንያት:
  • A. 

   መብላት፣ ለስላሳ መጠጥ መጠጣት ወይም ማጨስ

  • B. 

   የእጅ ስልክ መጠቀም እና/ወይም ቴክስት ማድረግ

  • C. 

   ሬድዮን፣ ሲዲን ወይም ቴፕን መቀየር

  • D. 

   ሁሉም መልስ ነው

 • 19. 
  በመንዳት ላይ እያሉ ድንዝዝ ካሉ(እንደማንቀላፋት ካረጎት) ማድረግ ያለቦት:
  • A. 

   ሊታገሉት መሞከር

  • B. 

   እረፍት መውሰድ

  • C. 

   "አንቅቶ የሚያቆይ" መድሀኒት መውሰድ

 • 20. 
  ለጎዳና ላይ ብስጭት ወይም ለሀይለኛ አነዳድ መንስኤ ሊሆን የሚችለው:
  • A. 

   በቅርቡ ጭራ ጭራን መከተል

  • B. 

   ደህንነት ባልተጠበቀ መልኩ መስመርን መቀየር

  • C. 

   ፍጥነት(ስፒዲንግ)

  • D. 

   ሁሉም መልስ ነው

 • 21. 
  በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ውስጥ በአንደ አቅጣጫ ብቻ የሚኬድበት(ዋን ሌን) መንገድ ላይ ሲጓዝ እና ወደ ሌላ በአንደ አቅጣጫ ብቻ የሚኬድበት መንገድ ወደ ግራ መታጠፍ ሲፈልገ፣ ቀይ የትራፊክ ምልክት ላይ ወደ ግራ መታጠፍ ህገ-ወጥ ነው።
  • A. 

   እውነት

  • B. 

   ሀሰት

 • 22. 
  ሀይዌዮች እና መንገዶች ከመሸጋገሪያዎች (ከራምፖች) እና ከድልድዮች ቀድመው በበረዶ ይያዛሉ(ፍሪዝ ያደርጋሉ):
  • A. 

   እውነት

  • B. 

   ሀሰት

 • 23. 
  እርጥብ መንገድ ላይ ሲነዱ፣ ማስታወስ ያለቦት:
  • A. 

   ዝናብ ከጣለ በሃላ ወዲያውኑ አስፋልት መንገድ የሚያሟልጭ ይሆናል

  • B. 

   እርጥብ መንገዶች ላይ መንዳት የጎማ መንሸራተትን(ሀይድሮፐላኒንግ) ሊያስከስት ይችላል

  • C. 

   ለማቆም ለእራሶ ተጨማሪ ግዜ መስጠት አለቦት

  • D. 

   ሁሉም መልስ ነው

 • 24. 
  ለመታጠፍ መፈለጎትን ምልክት ማሳየት ያለቦት ቢያንስ፡
  • A. 

   200 ጫማ

  • B. 

   150 ጫማ

  • C. 

   100 ጫማ

  • D. 

   50 ጫማ

 • 25. 
  ተሽከርካሪዎን ከመንሸራተት ለማውጣት፣ መጀመሪያ ማድረግ ያለቦት፡
  • A. 

   መሪውን ቀጥታ ወደፊት ያድርጉ

  • B. 

   መንሸራተቱ ካለበት ወደ በተቃራኒ አቅጣጫ መሪውን ያዙሩ

  • C. 

   መጓዝ በሚፈልጉበት አቅጣጫ መሪውን ያዙሩ

  • D. 

   ፍሬኑን በሀይል ይያዙ

×

Wait!
Here's an interesting quiz for you.

We have other quizzes matching your interest.